ቀጥታ፡

የአማራ ክልል ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2017(ኢዜአ):- የአማራ ክልል መንግስት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የክልሉ መንግስት ለኢሬቻ በዓል ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል:-

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ለመላው የኦሮሞ ህዝብ እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በሀገራችን የዘመን መለወጥን ተከትሎ ልዩ ልዩ በዓላትን በአደባባይ እያከበርን እዚህ ደርሰናል። ከእነዚህ በዓላት መካከል አንዱ በኦሮሞ ህዝብ በድምቀት የሚከበረውና የማንነቱ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ በዓል አንዱ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በአደባባይ የሚያከብረው የኢሬቻ በዓል የሰላምና የአንድነት ምልክት የሆነ፤ የኦሮሞ ህዝብ ከፈጣሪው ጋር ባለው ቁርኝት የልምላሜ ምንጭ የሆነውን የክረምቱን ዝናብ ለሰጠ ፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ዕለት እንደሆነ ይታወቃል።

ከዚህም በላይ ኢሬቻ አብሮነትና አንድነትን የማጠናከር ኃይል ያለው በዓል ነው። ስለሆነም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና በዓል እንዲሆን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መልካም ምኞት መግለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም