የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2017(ኢዜአ):- የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባ ከድር በኢሬቻ ቂም በይቅርታ ይሻራል፤ ጨለማ ለብርሀን እጁን ይሰጣል፤ በክረምት የተለያየ ህዝብ ይገናኛል፤ የተጣላ ሁሉ ታርቆ ጥላቻ ቦታ ያጣል ወንድማማችነት እህትማማችነት እና አብሮነት ይነግሳል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻችው ባሰፈሩት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል።

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም፥ በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም