ቀጥታ፡

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እና የሽግግር ደህንነት የቁጥጥር እና ማረጋገጫ ማዕቀፍ ሊቀ-መንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እና የሽግግር ደህንነት የቁጥጥር እና ማረጋገጫ ማዕቀፍ(CTSAMVM) ሊቀ-መንበር ሜጀር ጀነራል ይታያል ገላው ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በደቡብ ሱዳን ግጭትን ለማስቆም የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት መደገፍ እና በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ጁባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እና የሽግግር ደህንነት የቁጥጥር እና ማረጋገጫ ማዕቀፍ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እ.አ.አ በ2014 የተቋቋመ ነው።

ቀጣናዊ የአሰራር መዋቅሩ የደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት እና የሽግግር ደህንነት ማዕቀፎች ትግበራ ይቆጣጠራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም