ቀጥታ፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ብሔራዊ ቡድኑ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጋቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ሰዒድ ሀብታሙ፣ ፍሬው ጌታሁን እና አቡበከር ኑራ ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች ናቸው።

ሱሌይማን ሀሚድ፣ብርሃኑ በቀለ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ያሬድ ባዬ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ራምኬል ጀምስ፣ አስራት ቱንጆ እና ዳዊት ማሞ በተከላካይ ክፍል የሚገኙ ተጫዋቾች መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አማካይ ክፍል ላይ ጋቶች ፓኖም፣ ወገኔ ገዛኸኝ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ቢኒያም በላይ፣ አብነት ደምሴ እና ቢኒያም አይተን ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

መሐመድ ኑር ናስር፣ በረከት ደስታ፣ መስፍን ታፈሰ፣ አቤል ያለው፣ ከነዓን ማርክነህና ቸርነት ጉግሳ ጥሪ የተደረገላቸው የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች ናቸው።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ ጀምሮ ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ በአዲስ አበባ ከተማ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥቅምት 2 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም የ35ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ጋር ኮትዲቭዋር ላይ ያደርጋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ 8 እስከ አሁን ባደረጋችው ጨዋታዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 2 ለ 0 ሲሸነፍ፣ ከታንዛንያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ መለያየቱ የሚታወስ ነው።

ውጤቶቹንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ በምድቡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በስድስት ነጥብ ምድቡን እየመራ ይገኛል። ታንዛንያ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም