ቀጥታ፡

አምባሳደር ዳባ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለላኦ ሕዝቦች ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አቀረቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2017(ኢዜአ)፦ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ለላኦ ሕዝቦች ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ቶንግሎን ሲሶሊዝ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ዳባ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና እምቅ የእድገት አቅም ለፕሬዝዳንት ቶንግሎን ሲሶሊዝ ገለፃ ማድረጋቸው ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮችም ከላኦ ጋር ትብብሯን ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።


 

የላኦ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ቶንግሎን ሲሶሊዝ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና፣ በሐይድሮ ኤሌክትሪክ፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ላኦ 7 ሚሊየን ህዝብ ያላት በደቡብ ምስራቅ እስያ የምትገኝ ሀገር ስትሆን የግብርና እና የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል እምቅ አቅም ካላቸው የአካባቢው ሀገራት አንዷ ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም