ቀጥታ፡

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በይፋ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2017 (ኢዜአ):- የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የትግበራ ኮሚቴውን ስራ በይፋ አስጀምረዋል።

የትግበራ ኮሚቴው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ እና የተለያዩ ተቋማት አመራሮችን መያዙን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የሙከራ ንግድ ማስፈፀሚያ እቅድ እና የቀጣናው ረቂቅ ስትራቴጂ ዝግጅት ሂደት እንደሚገመገም ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም