በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር በጋራ ልንቆም ይገባል -ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር በጋራ ልንቆም ይገባል -ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ
ጋምቤላ፤ መስከረም 23/2017 (ኢዜአ)፦ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማት፥የህዝቡን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።
የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ዛሬ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሯ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ የክልሉ መንግስት የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በዋናነት በህዝቦች መካከል ያለውን ሰላም ማጽናት ከተቻለ የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ማሳካት እንደሚቻል አረጋግጠዋል።
በክልሉ የህዝቡን ህይወት እንዲቀይሩ ታስበው የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረትም የህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተለይም በህዝቦች መካከል ያለው ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር እሴቶች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የሁሉንም የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።
ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚሁ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የአመራር አካላትን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።