ኢትዮጵያ እና ቆጵሮስ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክሩ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ቆጵሮስ በኢኮኖሚ መስክ ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2017 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ እና ቆጵሮስ በኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከቆጵሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዘርፍ ዳይሬክተር ኤልኒ አፔይቱ ጋር በቆጵሮስ መዲና ኒኮሲያ ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
በሀገራቱ መካከል በፋርማሲቲዩካል ዘርፍ ያለውን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት በሌሎችም ዘርፎች ለማስፋት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
በቀጣይም የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማዘጋጀት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ኢዜአ ከሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።