ኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች ማህበራት ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን ጉባዔን ልታስተናግድ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች ማህበራት ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን ጉባዔን ልታስተናግድ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2017 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን የጭነት አስተላላፊዎች ማህበራት ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን (FIATA) ጉባዔን ለማስተናገድ መመረጧን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ጉባዔው በአዲስ አበባ ይደረጋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን ለማካሄድ መመረጧ በአፍሪካ አህጉር በሎጂስቲክስ ዘርፍ እየጎለበተ የመጣውን ሚናዋን በጉልህ የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊና የመርከብ አገልግሎት ወኪሎች ማህበር ይህን ጉባኤ በሀገሪቷ እንዲያዘጋጅ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተጠቁሟል።
በጉባዔው ላይ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ፤ የዘርፋ አመራሮች እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉበት ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።