ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የጆቡቲ አቻውን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከጂቡቲ አቻው ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት መንግስቱ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ናትናኤል ሰለሞን፣ ዳግም አወቀ እና ሰለሞን ገመቹ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጂቡቲ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የአቋም መለኪያ ጨዋታ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል።

ብሔራዊ ቡድኑ በታንዛንያ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ለመሳተፍ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም