ቀጥታ፡

አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በአፍሪካ የአምባሳደሮች ቡድን ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2017(ኢዜአ):- በቤልጂየም፣ ኔዘርላንድስ፣ ሉክሰምበርግ (ቤኔሉክስ) አገራትና በአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ተቀማጭነታቸውን ብራሰልስ ያደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን (GAAP) ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

ለ200ተኛ ጊዜ በተካሄደው ስብሰባ አምባሳደር እሸቴን ጨምሮ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች መሳተፋቸው ታውቋል።

አምባሳደር እሸቴ በስብሰባው ላይ ከአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች እና ተወካዮች ጋርም ተወያይተዋል።

ተቀማጭነታቸውን ብራሰልስ ያደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን (GAAP) ስብሰባ በየወሩ የሚካሄድ ሁነት ነው።

ስብሰባው የአፍሪካ ፍላጎቶች በአውሮፓ ሕብረት እና በሌሎች መድረኮች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግን አላማ ያደረገ መሆኑን ኢዜአ ቤልጂየም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም