ቀጥታ፡

የምስራቅ ዕዝ በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2017(ኢዜአ):- በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት  አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ፈቃዱ ጸጋዬ እጅ ተረክበዋል።

ድጋፉ ከምስራቅ ዕዝ ሰራዊት አባላትና ከተጨማሪ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች የተሰበሰበ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም