ኢትዮጵያ በካርቱም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በካርቱም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እንደምታወግዝ አስታውቃለች፡፡
ኢትዮጵያ በሱዳን ያሉ ሁሉም ወገኖች አለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ደንቦችን እንዲያከብሩና የዲፕሎማቲክ ሰራተኞችን እና ተቋማትን አደጋ ላይ ከሚጥል ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርባለች፡፡