በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽሬ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽሬ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም ተካሂዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ስሑል ሽሬ እና ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ አምስት ነጥብ በብዙ ጎል ባገባ መለያ ተበላልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም