በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 20/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ክለቦች መርሃ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ማምሻውን ተከናውኗል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን በመጀመሪያ የሊጉ ጨዋታው ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ መለያየቱ የሚታወስ ነው።
በአንጻሩ በዘሪሁን ሸንገታ የሚሰለጥነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የዛሬውን ሳይጨምር በሊጉ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ወጥቷል።
ቀን ላይ በተካሄደ የሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።