ቀጥታ፡

መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል

አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የፊት መስመር ተሰላፊው ያሬድ ብርሃኑ በ51ኛው ደቂቃ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱት ተከትሎ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ የተመለሰው መቀሌ 70 እንደርታ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ድሉን አግኝቷል።

በአንጻሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሌላኛው የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም