ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የመንግስትን አስተዳደር ማዘመን ስራ የሚውል የ70 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ገንዘቡ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ባለው የብድር አይነት (Concessional Loan) የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ማርያም ሳሊም ናቸው።

የፋይናንስ ስምምነቱ የመንግስትን አስተዳደር ማዘመን ውጤታማ አገልሎትን መስጠት አላማ ላደረገው ፕሮጀክት ትግበራ የሚውል እንደሆነ ተመላክቷል።

የሕዝብ አስተዳደር አቅምን ማጎልበት፣ አገር በቀል የገቢ መሰብሰብ አቅምን ማሳደግ እና የሕዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን ማሻሻል የፕሮጀክቱ ዋንኛ የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም