ቀጥታ፡

የቡና ምርታማነትንና ጥራትን ለማሳደግ አምራቾች በቅርበት ይደገፋሉ -አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2017(ኢዜአ):-  የቡና ምርታማነትና ጥራትን ለማሳደግ አምራቾች በቅርበት ይደገፋሉ  ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን  ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመተባበር በነቀምቴ ከተማ የቡና ምርታማነት፣ እድገትና ጥራት ማሻሻያ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡


 

በንቅናቄው ላይ የተገኙት  የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፤  የቡና ምርታማነትንና ጥራትን ለማሻሻል ኢንሼቲቭ ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ባለፉት ዓመታት በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን የመትከል፣ የማደስና ሌሎች ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ የቡና ምርታማነት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

ነገር ግን  ጥራት ከማሻሻል አንጻር የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የቡና ምርታማነት እና ጥራትን ለማሳደግ አምራቾች በቅርበት ይደገፋሉ ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ መንግስት ከሚያከናውነው ስራ በተጨማሪ አምራቾች ፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች እንዲሁም የምርምር ተቋማት በቅንጅት እና በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም