ቀጥታ፡

የበርሊን ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2017(ኢዜአ)፦  በበርሊን የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አራት በመውጣት አሸንፈዋል ።

በወንዶች  ማራቶን አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ አሸንፏል፡፡ 

የበርሊን የሴቶች ማራቶን አትሌት ትዕግስት 42 ኪሎ ሜትሩን ለመፈጸም 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ   በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆን ችላለች ።

አትሌት መስታወት ፍቅር ሁለተኛ  ፣  ቦስና ሙላቴ ሶስተኛ ፣  አትሌት አበሩ አያና አራተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል::

በወንዶች  የበርሊን ማራቶን ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ አሸንፏል።


 

አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግባት በአንደኝነት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።

በርሊን ማራቶን ዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠው የማራቶን ውድድር ነው 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም