ኢትዮጵያ በሶማሊያ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 19/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሐዘን መግለጫ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዘ ሽብርተኝነትን በመታገል ረገድ ከሶማሊያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኑንም አረጋግጧል፡፡