የቡና ምርታማነትና ጥራት ማሻሻያ የንቅናቄ መድረክ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቡና ምርታማነትና ጥራት ማሻሻያ የንቅናቄ መድረክ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2017(ኢዜአ)፦ የቡና ምርታማነትና ጥራት ማሻሻያ የንቅናቄ መድረክ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በንቅናቄው ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና በቡና ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) የቡና ጥራት ማስጠበቂያ ሰነድ አቅርበዋል።
በአገሪቱ የቡና ምርት እያደገ መምጣቱን አንስተው ይህንን ለማስቀጠል አምራቾች፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች በቅንጅት እንዲሰሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የመስከረም ወር የቀይ ቡና ለቀማ በአብዛኛው በቡና አብቃይ አካባቢ የሚጀመርበት ወር መሆኑን ጠቅሰው አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
የቡና አምራች አርሶ አደሮች እና ቀይ ቡና የሚያዘጋጁ ኢንዱስትሪዎች ጥራቱን የተጠበቀ ምርት ለማምረት መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል።