ቀጥታ፡

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም በድካም ያረፉበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመቄዶኒያ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2017(ኢዜአ)፦ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም በድካም ያረፉበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር የገንዘብ ድጋፍና የማእድ ማጋራት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፅዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ አለም ድካም ያረፉበት አደኛ ዓመት በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ታስቦ ውሏል።

የሊቀ ጳጳሱ ብጹዕ አቡነ ሰላማ አህት የሆኑት ወይዘሮ ዘውዱ አድሃኖም፤ በመቄዶኒያ በመገኘት የ400 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍና ማዕድ አጋርተዋል።


 

የሊቀ ጳጳሱን እረፍት አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያን ድጋፍና ማእድ በማጋራታችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

በመሆኑም ሌሎች ወገኖችም የሃዘን፣ የሰርግና ሌሎችም ፕሮግራሞችን በመቄዶኒያ በማድረግ ወገኖቻቸውን አንዲያግዙ ጠይቀዋል።

የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ፤ በብዑዕ አቡነ ሰላማ ስም ለተደረገው የማእድ ማጋራት ምስጋና አቅርበዋል።


 

የደስታም ሆነ የሃዘን ድግሶችን በማዕከሉ በማሳለፍ ጧሪ የሌላቸውን አረጋውያን ሌሎችም ወገኖች እንዲደግፍ ጠይቋል።

ብጹዕ አቡነ ሰላማ የአክሱም ርዕሰ አድባራት ሊቀጳጳስ፤ በምስራቅ ሀረርጌ የሃረር አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በአዲስ አበባ ደግሞ የታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም እና ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም