ቀጥታ፡

የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የተፋሰሱን አገራት በጋራ የማደግ እና የመበልፀግ ሕልም እውን የሚያደርግ ነው- አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2017 (ኢዜአ)፦ የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የተፋሰሱን አገራት በጋራ የማደግ እና የመበልፀግ ሕልም እውን እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

አምባሳደር ታዬ በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ማዕቀፉ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ሊገባ መቃረቡን ገልጸዋል።

ስምምነቱ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያሰፍን ነው ብለዋል።

የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የተፋሰሱን አገራት በጋራ የማደግ እና የመበልፀግ ሕልምን እውን የሚያደርግ ታሪካዊ ማዕቀፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ስምምነቱን ያልፈረሙ አገራት ስምምነቱን በማፅደቅ ለማዕቀፉ ውጤታማነት ድጋፍ እንዲያደርጉ አምባሳደር ታዬ ጥሪ አቅርበዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከኢትዮጵያ የኢነርጂ ኃይል የማግኘት ፍላጎትና በቀጣናው ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መሻት የመነጨ ነው ብለዋል።

ሕዳሴ ግድብ በቀጣናው ትስስርና ትብብርን የማጎልበት ጉልህ ፋይዳ እንዳለውም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም