የደመራና የመስቀል በዓል በጎንደርና በሰቆጣ ከተሞች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የደመራና የመስቀል በዓል በጎንደርና በሰቆጣ ከተሞች እየተከበረ ነው

ጎንደር/ ሰቆጣ፤ መስከረም 17/2017(ኢዜአ)፦ የደመራና የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊትና ስርአቱን በጠበቀ መንገድ በጎንደርና በሰቆጣ ከተሞች እየተከበረ ነው።
በዓሉ በጎንደር ከተማ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በከተማው መስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ግርማይ ልጃለም ተገኝተዋል።
ከከተማው አድባራትና አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ ዲያቆናትና ቀሳውስትም ግማደ መስቀሉ የተገኘበትን እለት የሚያበስሩ ያሬዳዊ ዝማሬዎችን በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተውታል።
በተመሳሳይ በዋግ ኽምራ ብሔብረሰብ አስተዳደርም የደመራና የመስቀል በዓል ከማለዳው ጀምሮ እየተከበረ ነው።
በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ባለው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ የዋግ ኽምራ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስን ጨምሮ በርካታ የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።