ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ ባደረጉት ጨዋታ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ ባደረጉት ጨዋታ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ ከእረፍት መልስ ጋናዊው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ ሀፊዝ ኮንኮኒ እና የኢትዮ ኤሌክትሪኩ የፊት መስመር ተሰላፊ ፍቃዱ ዓለሙ ያገኟቸውን ግልጽ የግብ እድሎች አምክነዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን ሊያሸንፍበት የሚችልባቸውን የግብ እድሎች ቢያገኝም ሊጠቀምባቸው አልቻለም።
አብዱላዚዝ አማን እና በፍቃዱ አስረሳኸኝ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም በፍቃዱ አለማየሁ ከኢትዮጵያ ቡና የቢጫ ካርድ ተመልክተዋል።
ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና መቀሌ 70 እንደርታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።