ቀጥታ፡

የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የ2017 የመስቀል ደመራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፀጥታና ደህንነት አካላት ከሕዝቡ፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ከወጣቶች ጋር በመሆን ባከናወኑት የቅንጅት ስራ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መከበሩን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕብረተሰቡ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ወጣቶችና የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች በዓሉ እንዲከበር ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

ሕብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ያሳየውን ትብብር በቀጣይ በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ የሆራ አርሰዴ በሚከበሩት የኢሬቻ በዓላት ላይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም