ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ከንቲባ አዳነች የአዲስ አበባ አንዱ ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ውብ፣ ደማቅና ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ እና በ2 ሺህ 575 የተለያዩ አድባራትና ቦታዎች ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ ሆኖ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ የሃይማኖት አባቶች፣ የከተማዋ ወጣቶች፣ በየደረጃው ሲያስተባብሩ የነበሩ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ ኃይሎችና የከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።