ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ ከሩዋንዳ ብሄራዊ ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል ሲጂ ፌሊክስ ናሙሆራንዬ ጋር በኪጋሊ ተወያይተዋል።

ውይይቱም በሁለቱ ሀገራት የፖሊስ ተቋማት መካከል ያለውን የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የሩዋንዳ ብሔራዊ ፖሊስ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በቅርቡ እንደሚፈራረሙ ተመላክቷል።

ምክትል ኮሚሽነር ነብዩ ዳኜ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ስምምነቱን አስመልክቶ ያዘጋጁትን የግብዣ ደብዳቤ ለሩዋንዳ ብሔራዊ ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል ሲጂ ፌሊክስ ናሙሆራንዬ ማስረከባቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም