በዓሉን ስናከብር ፍቅራችንንና አንድነታችንን በማጎልበት የጋራ ማህበራዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ለመሻገር የጀመርናቸውን ተግባራት በማጠናከር መሆን አለበት - ከንቲባ ከድር ጁሃር - ኢዜአ አማርኛ
በዓሉን ስናከብር ፍቅራችንንና አንድነታችንን በማጎልበት የጋራ ማህበራዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ለመሻገር የጀመርናቸውን ተግባራት በማጠናከር መሆን አለበት - ከንቲባ ከድር ጁሃር
ድሬደዋ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከብር የእርስ በርስ ፍቅራችንንና አንድነታችንን በማጎልበት የጋራ ማህበራዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ለመሻገር የጀመርናቸውን ተግባራት በማጠናከር መሆን አለበት ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።
ከንቲባ ከድር ጁሃር ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የመስቀል ደመራ በዓል በአደባባይ ከሚከበሩ ድንቅ እና አለም አቀፍ ዕውቅና ከተቀዳጁ በአላቶቻችን አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
በዓሉን ስናከብር የእርስ በርስ ፍቅራችንንና አንድነታችንን፤ የጋራ ማህበራዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ለመሻገር የጀመርናቸውን ተግባራት በማጠናከር መሆን አለበት ብለዋል።
ህዝበ ክርስቲያኑ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ስኬታማ እንዲሆኑ እያበረከቱት የሚገኘው አስተዋፅኦ ተጠቃሽ መሆኑን አክለዋል።
በዓሉን ስናከብር በዘንድሮ አመት የተወጠኑትም የሰላም እና የልማት ስራዎችን ዳር ለማድረስ በመነሳሳት መሆኑን እንዳለበትም በመጥቀስ።
በተጨማሪም ድሬዳዋ የምትታወቅበትን የበጎ ፍቃድ ስራዎች በበጋ ወራትም በማስቀጠል እና ለተቸገሩ ማዕድ የማካፈሉን ስራ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ከንቲባው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆንም ተመኝተዋል።