የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች መከበር ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች መከበር ጀመረ።
በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብጹዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።
በተጨማሪም የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የእምነቱ ተከታዮች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎችም በበዓሉ ተገኝተዋል።
የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር ትልቅ የአደባባይ በዓል ነው።
በዓሉ ከዋዜማው አንስቶ በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላትም አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የምትደምረው ደመራ የራሱ አንድምታም አለው።
የመስቀል ደመራ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) እውቅና ተሰጥቶት በዓለም አቀፍ ቅርስነት ተመዝግቧል።