ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በባህል ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ትሰራለች - አምባሳደር ገነት ተሾመ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በባህል መስክ ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጎልበት እንደምትሰራ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ገለጹ።

አምባሳደር ገነት በሞስኮ የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎችና መምህራን በሌኒን ቤተ-መጻሕፍት የምሥራቅ የሥነ-ጽሁፍ ማዕከል ኢትዮጵያን በማስመልከት ያዘጋጁትን የስነ-ጽሁፍና የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

አምባሳደር ገነት ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸውን ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸው አመልክተዋል።


 

በሞስኮ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሩሲያዊያንና መምህራኖቻቸው የኢትዮጵያን ባሕልና ስነ-ጥበብ ለሩሲያ ዜጎች ለማስተዋወቅ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።

በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከትምህርት ተቋማቱ፣ ከማዕከሉና ከተማሪዎቹ ጋር በተለያዩ መርሃ ግብሮች በትብብር እንደሚሰራ አምባሳደሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኤምባሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም