የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ይከበራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ይከበራል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2017(ኢዜአ):- የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት አስታወቀ።
ሕብረቱ በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ የሆራ አርሰዲ የሚከበረውን ኢሬቻ በዓል አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም፤ በመስከረም 25 ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ፤ በመስከረም 26 ደግሞ ኢሬቻ ሆረ አርሰዴ እንደሚከበር ተገልጿል።
የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የመጫ አባ ገዳ ወርቅነህ ተሬሳ እንዳሉት የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል።
የእርቅ፣የሰላም እና የአንድነት በዓል በሆነው ኢሬቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲያከብረው ጥሪ አቅርበዋል።