በአምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እየተሳተፈ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እየተሳተፈ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2017 (ኢዜአ)፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።