አፍሪካውያን የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት በጋራ መስራት አለባቸው - አምባሳደር አሳየ አለማየሁ - ኢዜአ አማርኛ
አፍሪካውያን የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት በጋራ መስራት አለባቸው - አምባሳደር አሳየ አለማየሁ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2017(ኢዜአ)፦አፍሪካውያን የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው በጋና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር አሳየ አለማየሁ ገለጹ።
ኢትዮጵያ የጋና የቀድሞ የነጻነት ታጋይና ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንክሩማህ የመታሰቢያ ቀንን በማስመልከት በመዲናዋ አክራ በተካሄደ ፌስቲቫል ላይ ተሳትፋለች።
በክዋሜ ንክሩማህ መታሰቢያ ፓርክ በተዘጋጀው ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች፣ መጠጦችና አልባሳትና የቡና አፈላል ስነ ስርዓት ተዋውቀዋል።
የፌስቲቫሉ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾችና ጥበባዊ ስራዎች እንዲሁም የባህል የሙዚቃ መሳሪያዎችንም ጎብኝተዋል።
በጋና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር አሳየ አለማየሁ ፌስቲቫሉን አስመልክቶ ከጋና መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሁለቱ አገራት ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ይህን ለረጅም ጊዜ የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር ትሰራለች ብለዋል።
አፍሪካውያን የአፍሪካን አንድነት በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት በትብብር መስራት እንዳለባቸው አምባሳደሩ መናገራቸውን ኢዜአ ጋና ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያና ጋና በፓን አፍሪካኒዝም መነሻነት ጠንካራ ወዳጅነት የፈጠሩ አገራት