ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ከቤልጂየም ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት ትሰራለች - አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ከቤልጂየም ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት ትሰራለች - አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ከቤልጂየም ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት በትኩረት እንደምትሰራ በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ገለጹ።
አምባሳደር እሸቴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለቤልጅየም የፌዴራል ፐብሊክ ሰርቪስ የውጭ ጉዳይ፣ የውጭ ንግድና ልማት ትብብር የፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ሁበርት ሮይሲን አቅርበዋል።
በአገልግሎት ዘመናቸው ከምዕተ-ዓመት በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያና የቤልጅየምን የሁለትዮሽ ግንኙነትና በተለያዩ መስኮች ያላቸወን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አምባሳደር እሸቴ ገልጸዋል።
የፕሮቶኮል ሹሙ አምባሳደር ሁበርት ሮይሲን መንግስታቸው አምባሳደሩ የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ለሚያከናውኑት ስራ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።