ቀጥታ፡

የቬትናም የጨርቃጨርቅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ማስፋት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2017 (ኢዜአ):- የቬትናም የጨርቃጨርቅ ኩባንያ ሺን ቴክስታይልስ ሶሉሽንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት ማስፋት እንደሚፈልግ አስታወቀ።

በኮሪያ ሪፐብሊክና ቬትናም የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ኩባንያው የሚያመርታቸውን የጨርቃጨርቅ፣አልባሳትና የተለያዩ ምርቶች ጎብኝተዋል።

የኩባንያው አመራሮች ለአምባሳደሩ ስለ ኩባንያው የስራ እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ሺን ቴክስታይልስ ሶሉሽንስ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት እንዲያስፋፋ ጥሪ አቅርበዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት ለማስፋት እየሰራ እንደሚገኝ መግለጹን ኢዜአ በኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሺን ቴክስታይልስ ሶሉሽንስ በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክ የጨርቃጨርቅ፣አልባሳትና የተለያዩ ምርቶችን እያመረተ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም