ኢትዮጵያ በፓኪስታን የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በፓኪስታን የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በፓኪስታን ካይበር ፓክቱንክዋ ግዛት የደረሰውን የሽብር ጥቃት አውግዛለች።
ጥቃቱ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶችን የያዘ ተሽከርካሪ ላይ መፈጸሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ በነበረው የፖሊስ ኦፊሰር ህልፈት ለቤተሰቦች፣ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግስት መጽናናትን እንደምትመኝ ገልጿል።