የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ " ጋሪ ዎሮ " በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ " ጋሪ ዎሮ " በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
           አዲስ አበባ፤መስከረም 12/2017(ኢዜአ)፦የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ " ጋሪ ዎሮ " በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
በዓሉ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው።
የብሔረሰቡ አባላት በየዓመቱ የአዲስ ዓመት መግባትን ተከትሎ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብሩት የዘመን መለወጫ በዓል "ጋሪ ዎሮ" ይባላል፡፡
ጋሪ ዎሮ ስለ ህዝቦች አብሮነት ፣ሰላም እና አንድነት የሚነገርበት እንዲሁም ከፈጣሪ ምህረት የሚለመንበት በዓል መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።
የሺናሻ ብሔረሰብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡
በተያዘው የመስከረም ወር በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን በተለያዩ ቦታዎች በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ለአብነትም በዛሬው ዕለት ከቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ በተጨማሪ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል " ዮዮ ጊፋታ " በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።