ቀጥታ፡

የወላይታ ሕዝብ አሮጌውን ዘመን ሸኝቶ አዲሱን የሚቀበልበት ''ዮዮ ጊፋታ'' በዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12/2017 (ኢዜአ)፦የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ዮዮ ጊፋታ" በዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

ጊፋታ የወላይታ ሕዝብ አሮጌውን ዘመን ሸኝቶ አዲሱን የሚቀበልበትና ተራርቀው የቆዩ ዘመድ አዝማድ ተገናኝተው በፍቅር የሚያከብሩት በዓል ነው።

በጊፋታ በዓል በይቅርታና ቂም ቁርሾን በማስወገድ እንዲሁም ስጦታን በመለዋወጥና አቅመ ደካሞችን በመርዳት አዲሱን ዘመን የሚቀበልበትም ነው ብለዋል።


 

ጊፋታ መደጋገፍና መተሳሰብ ጎልቶ የሚታይበት የተቀያየሙና የተቃቃሩ የሚታረቁበት፣ ቂምና ቁርሾ ያላቸው በጊፋታይቅር ተባብለው አዲሱን ዓመት በንፁህ ልቦናና በፍጹም ደስታ ይቀበሉታል።

በዓሉ ያለምንም ልዩነት ከጎረቤትና አጎራባች ህዝቦች ጋር በመሆን ዘመንን ያሸጋገረ አምላክ የሚመሰገንበትና በመጪው ጊዜ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል አብሮነት የሚገነባበት ዕሴት ጭምር ነው።

በዛሬው ዕለትም  የጊፋታ በዓል ለማክበር ሕዝቡ ወደ ወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በመግባት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም