የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም በረራ የጀመረበት 60ኛ ዓመት በጣልያን ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም በረራ የጀመረበት 60ኛ ዓመት በጣልያን ተከበረ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም በረራ የጀመረበት 60ኛ ዓመት በጣልያን መዲና ሮም ተከብሯል።
በመርሐ ግብሩ ላይ በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ፣ በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አጉስቲኖ ፓሌሴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ ተገኝተዋል።
የ“Aeroporti di Roma”(ADR) ኤርፖርት ኦፕሬሽን ኃላፊዎች፣ በሮምና ሚላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአከባበሩ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።
አየር መንገዱ ወደ ሮም በረራ የጀመረበትን 60ኛ ዓመት በአዲስ አበባ ማክበሩ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም የመጀመሪያ በረራውን ያደረገው እ.አ.አ ሰኔ 5 1964 ነበር።
አየር መንገዱ ከሮም በተጨማሪ ወደ ሌላኛዋ የጣልያን ከተማ ሚላን እ.አ.አ በ2011 በረራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።