ቀጥታ፡

ሀዲያ ሆሳዕና በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ድል ቀናው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2017(ኢዜአ)፦ በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና አምበልና የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ሄኖክ አርፊጮ በዘጠነኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ጋር ያዋሃዳት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ሄኖክ የሊጉን የመጀመሪያ ጎልም አስቆጥሯል።

የጨዋታ ዋና ዳኛ ተፈሪ አለባቸው የሀዲያ ሆሳዕናውን የአማካይ ተጫዋች አስጨናቂ ፀጋዬን በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ አሰናብተውታል።

የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ በአርባ ምንጭ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ መካከል ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም