ቀጥታ፡

አየር መንገዱ ወደ ወደብ ከተማዋ ጉዋንዡ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ጉዋንዶንግ ግዛት በምትገኘው የወደብ ከተማ ጉዋንዡ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 ከፍ ማድረጉን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ወደ ከተማዋ ሰባት ሳምንታዊ በረራዎች ሲያደርግ መቆየቱንና ከመስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ ሶስት በረራዎችን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ቤጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ቼንግዱና ሆንግ ኮንግ አየር መንገዱ በቻይና በረራ የሚያደርግባቸው ሌሎች ከተሞች ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 139 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች እንዲሁም 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም