የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

ሽልማቱ የተበረከተው ኮርፖሬሽኑ 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት መርሓ ግብር ላይ ሲሆን አየር መንገዱ ላበረከተው የላቀ አገልግሎት እና የላቀ የስራ አጋርነት ዕውቅና የተሰጠበት መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

ይህ ሽልማት ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛ እና በዕቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም