የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 23 ጀምሮ ወደ አቴንስ የሚያደርገውን በረራ ሊያሳድግ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 23 ጀምሮ ወደ አቴንስ የሚያደርገውን በረራ ሊያሳድግ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያሳድግ አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ አራት ጊዜ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ በሳምንት ስድስት ቀን እንደሚያደርግ ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡