በአዲስ አበባ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2017(ኢዜአ):- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በመሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስጀመራቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።