በህዝቦች መካከል የመደጋገፍ ባህል እንዲጎለብትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
በህዝቦች መካከል የመደጋገፍ ባህል እንዲጎለብትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2017(ኢዜአ):- በህዝቦች መካከል የመደጋገፍ ባህል እንዲጎለብትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የብሔራዊ መውሊድ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸኽ ፈቱውዲን ሃጂ ዘይኑ ጥሪ አቀረቡ፡፡
1ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት መውለድ በዓል በታላቁ አኑዋር መስጂድ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የብሔራዊ መውሊድ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸኽ ፈቱውዲን ሃጂ ዘይኑ የዘንድሮው መውሊድ "የሠላሙ ነቢይ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ጋር በማስተሳሰር እየተከበረ መሆኑን ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ የሙስሊም ማህበረሰብ ከሃይማኖታዊ ጉዳይ በተጨማሪ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ ተቋም በመሆን እንዲያገለግል አስተዋጽኦ ላደረጉ እና እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና አቅረበዋል።
ምክር ቤቱ የነብዩ መሀመድ አስተምህሮት እና ተምሣሌት ለሀገር ሠላም እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በህዝቦች መካከል የመደጋገፍ ባህል እንዲጎለብትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡