1ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
1ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2017(ኢዜአ):- 1ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ የሀይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።
በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ያለውን በዓል የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጣኻ ሀሩን ቁርአን በመቅራትና ዱዓ በማድረግ በይፋ የሚያስጀምሩት ይሆናል።
በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በታላቁ አኑዋር መስጂድ በሰደቃ፣ በመንዙማና በነሺዳ በሀይማኖት አባቶች በወጣቶች እና በታዳጊዎች መርሐ ግብር የሚከበር ይሆናል።