የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2024 የአፍሪካ የላቀ የቱሪዝም ትራንስፖርት ሽልማት ተበረከተለት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2024 የአፍሪካ የላቀ የቱሪዝም ትራንስፖርት ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2017(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦትስዋና ጋቦሮኒ በተካሄደው የ2024 የአፍሪካ ቱሪዝም አመራር ፎረም ላይ “የላቀ የቱሪዝም ትራንስፖርት ሽልማት” ተበርክቶለታል።
ሽልማቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመንገደኞች በማቅረብ እንዲሁም ዘላቂነት እና የአየር ንብረት ጥበቃ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ ለአፍሪካ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ድርጅቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።