የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር ዋይድ አዋርድ 2016 ‘ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋም’ በመባል ተሸላሚ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር ዋይድ አዋርድ 2016 ‘ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋም’ በመባል ተሸላሚ ሆነ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር ዋይድ አዋርድ 2016 ‘ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋም’ በመባል በሕዝብ ድምፅ ተሸላሚ ሆኗል።
ሽልማቱን አስመልክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሽልማት ርክክብ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ሽልማት የሚያስደስተን ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ለላቀ ደረጃ በትጋት እንድንሰራ የሚደግፈን ነው ብለዋል።