ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ አገልግሎት ሁነት ላይ የቱሪዝም መስህቦቿንና የወጪ ምርቶቿን እያስተዋወቀች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ አገልግሎት ሁነት ላይ የቱሪዝም መስህቦቿንና የወጪ ምርቶቿን እያስተዋወቀች ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የንግድ አገልግሎት ሁነት ላይ የቱሪዝም መስህቦቿንና የወጪ ምርቶቿን በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች።
በቻይና ከሚገኙ ግዙፍ የንግድ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው የንግድ ትርኢት “ዓለም አቀፍ አገልግሎት፣ ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።
በንግድ አገልግሎት ሁነቱ ላይ ኢትዮጵያ ቤጂንግ በሚገኘው ኤምባሲዋ ተወክላ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ነች።
በሁነቱ ላይ የኢትዮጵያ የቱሪስት መስህቦችን፣የወጪ ምርቶችና የቡና አፈላል ስነ ስርዓት የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከሁነቱ ጎን ለጎን በሚካሄዱ ፎረሞች ላይ ትሳተፋለች።
ዓለም አቀፍ የንግድ አገልግሎት ሁነቱ እስከ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።